Choose your meal
በግ እግር አሮስቶ Recipe Ingredients ► 1 ሙሉ የበግ እግር
► 4 ፍሬ ነጭ ሽንኩርት
► 2 ፍሬ ቀይ ሽንኩርት
► 2 ግንድ የጥብስ ቅጠል
► 1 ፍሬ ሎሚ
► 1 ብርጭቆ ውሃ
► 4 ፍሬ ድንች
► 1 የቡና ስኒ ዘይት
► ጨውና ቁንዶ በርበሬ
Process ■ የበግ ስጋውን በደንብ ማጠብ፣
■ ነጭ ሽንኩርት ልጦ፣ አጥቦ በረጃጅሙ መከታተፍ፣
■ የጥብስ ቅጠሉን በትንንሽ መቆራረጥ
■ የበጉን ስጋ ቢላ በመጠቀም ቀዳዳ ማበጀት፣
■ ነጭ ሽንኩርትና የጥብስ ቅጠሉን የተቀደደውን የበግ ስጋ ውስጥ መጨመር፣
■ ቀይ ሽንኩርቱን ልጦ አጥቦ ለ 4 መቆራረጥ
■ ድንች ልጦ ፣ አጥቦ ለ 4 መቆራረጥ
■ የላዛኛ ዕቃ ላይ የበጉን እግር ውሃ እና ዘይት ጨምሮ በአልሙኒየም ፎይል ከድኖ በ 250 ዲግሪ በጋለ ኦቨን ውስጥ ለ 1 ሰዐት ከ 30 ደቂቃ ያህል ማብሰል፣
■ የበሰለውን የበግ እግር ከኦቨን አውጥቶ የተቆራረጡትን ሽንኩርትና ድንች አስገብቶ ጨውና ቁንዶ በርበሬ ነስንሶ የአልሙኒየም ፎይል ሳይከድን በ 250 ዲግሪ በጋለ ኦቨን ውስጥ ጨምሮ ለ30 ደቂቃ ያክል አብስሎ ማውጣት እና አቀዝቅዞ ማቅረብ።

