■ በጎድጓዳ ሳህን ውስጥ ማር፣ ሶያ ሶስ፣ ውሃ እና ካቻፕ ጨምሮ በደንብ ማዋሀድ፣ ■ ነጭ ሽንኩርት ልጦ አጥቦ በደቃቁ መክተፍ፣ ■ በርብሬ፣ ጦስኝ፣ ቁንዶ በርበሬ እና ነጭ ሽንኩርትን ከማርና ሶያ ሶስ ጋር ደባልቆ ማዋሀድ፣ ■ የዶሮውን ታፋ በደንብ አጥቦ፣ ውህዱ ውስጥ ዘፍዝፎ ማስቀመጥ (ለ2 ደቂቃ) ■ ድንቹን ልጦ አጥቦ በረጃጅሙና በወፍራሙ መክተፍ ■ ካሮቱን ልጦ አጥቦ በረጃጅሙና በወፍራሙ መክተፍ ■ ፎሶሊያውን አጥቦ ጫፉና ጫፉን ቆርጦ ለ 2 መሰንጠቅ ■ በጎርጓዳ ድስት ውስጥ ዘይት አግሎ ዶሮውን ከተዘፈዘፈ ውህዱ አውጥቶ መጥበስ፣ ካሮቱን ወደ ዶሮው ጨምሮ በደንብ አንድ ላይ መጥበስ ፣ ■ የሚጠበሰው ዶሮና ካሮት ውስጥ የተከተፈውን ድንችና ፎሶሎያ ጨምሮ መጥበስ፣ ■ ለትንሽ ደቂቃ ከተጠበሰ በኋላ የማርና ሶያ ሶሱን ውህድ ጨምሮ በደንብ ለ20 ደቂቃ ማንተክተክ፣ ■ እየበሰለ እያለም የመድረቅ ባህሪ ካሳየ ሙቅ ውሃ ጠብ እያደረጉ ማብሰል ከበሰለ በኋላ ጨውና ቁንዶ በርበሬ ጨምሮ ማውጣት፣ ■ የተዘጋጀውን ዶሮ ከበሰለ ነጭ ሩዝ ጋር ደባልቆ ማቅረብ።
|